DW Amharic የዓለም የምግብ መርሃ ግብር በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ለሥራው ትልቁ የፀጥታ ሥጋት ያለበት አካባቢ አማራ ክልል መሆኑን ዛሬ አስታውቋል። የሌሎች ክልሎች የፀጥታ ሁኔታም ለስራው አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ፌደሬሽን ፣በኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ላይ ክስ እመሰርታለሁ ብሏል። ፌደሬሽኑ እንዳለው በሰሜን ኢትዮጵያው የርስ በርስ ጦርነት ወቅት ላጓጓዛቸው የሎጂስቲክ አቅርቦቶች ሊከፈለኝ ይገባ ነበር ያለው ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ አልተሰጠውም።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ያሉት ልዩነቶች፣ በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪዎች መካከል እንጂ ፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር የሚገናኝ አይደለም ብሏል። የአዲስ አበባ አስተዳደር የከተማይቱን የትራፊክ መጨናነቅ ለማስቀረት መፍትሄ ያለውን እቅድ አቅርቧል። እነዚህ የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው።
Ещё видео!