ተራኪዎች
ብሌን ሳሙኤል..
.አንተነህ አስረስ የዉብዳር
ኤርሚያስ ገ ሚካኤል
ምስልና ድምፅ ዉህደት አምባዉ ደሳለኝ
" ስሌት " የተሰኘዉን አጭር ልብወለድ ደራሲ ብሌን ሳሙኤል ። በማህበራዊ ትስስር ገጿ ላይም በርካታ የእንግሊዘኛ እናም የአማርኛ ግጥሞችን ለግጥም አፍቃሪያን በመከተብ ትታወቃለች ። አሁን ደግሞ በ አጭር ልብወለድ ዘዉግ ስሌት የሚለዉን ስራ ይዛልን መጥታለች ። ከዚህም ቀደም " አንዳንድ ሌሊቶች " የሚል የ አጭር ልብወለድ የውርስ ትርጉም ስራ እንደሰራች መዘንጋት አንችልም ። ከዚህም በተጨማሪ ከተለያዩ የጥበብ ሰዎች ጋር በመዋሀድ ፈታኝ የሚባሉ ጠንካራ የገጸ ባሕሪያት ዘዉግ ያላቸዉን መጽሐፎች በተስገምጋሚ ድምጽ ተርካልናለች ። ለአበይትነት ከተረከቻቸዉ በርካታ መጽሐፎች ውስጥ ለመጥቀስ ያህል ፤ የደራሲ ደረጄ በቀለ ህያው ፍቅር ፥ የበዓሉ ግርማ ደራሲው የተሰኘውን ፤ እንዲሁም የደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደን እና የ አዳም ረታ በርካታ አጫጭር ልብ ወለዶች በወርቃማ ትንፋሸ ወ ድምጿ በመተረክ ትታወቃለች ። ብሌን ሳሙኤል ደራሲ ፥ ገጣሚ ፥ ተራኪ ፥ እንዲሁም ዳይሬክተር በመሆን የተለያዩ ስራዎች ላይ ተሳትፋለች ።
Ethioemma april 2023
Ещё видео!