+ Live ኑ አብረን እንፀልይ | ረቡዕ | ፀሎተ ባርቶሥ ህዳር 25 || 04 December 2024
💚💛❤ፀሎተ ባርቶስ ምንድን ነው?💚💛❤ ጸሎተ ባርቶስ ስያሜውን ያገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በባርቶስ ሀገር ስለጸለየችው፤ ጸሎተ ባርቶስ ወይም ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም ዘሀገረ ባርቶስ ተብሎ ተጠርቷል። እመቤታችን ሦስት ጸሎቶችን በመዓዛ መለኮት በጣፈጠ ጥዑም አንደበት ፀልያለች። 1ኛው) በሉቃስ ወንጌል 1÷46-55 ድረስ ያለው ፀሎተ እግዝእትነ ማርያም የምንለው ነው። 2ኛው) በሰኔ 21 ቀን በጎልጎታ የጸለየችውና ቃልኪዳን የተቀበለችበት ፀሎት ነው። ይህም ''የሰኔ ጎለጎታ'' ተብሎ የሚጠራው ነው። 3ኛው) ይህ ጸሎተ ባርቶስ ነው። ከነዚህ መካከል ጸሎተ ባርቶስ የሚለየው እንደ ውዳሴ ማርያም የዘወትርና የእለት ያለው መሆኑ እና እንዲሁም ጸሎቱ በውስጡ አጋንንትን የሚያርቅ፣ የሚያስደነግጥ፣ የሚቆራርጥ ኅቡዕ ስሞች (ስውር የአምላክ ስሞች) የያዘ መሆኑ ነው። እመቤታችን በዚህ ታላቅ ጸሎት ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ የጌታን ወንጌል በማስተማሩ በጽኑ እስራት እና መከራ ውስጥ ወድቆ ስለነበር እሱንም ከእስር ያስፈታችው በዚህ ፀሎት ነው። እመቤታችን ይህንን ጸሎት ስትጸልይ በጸሎቱ ኃይል መሬት ተንቀጥቅጧል፣ መቃብራት ተከፍተዋል፣ ሙታን ተነስተዋል፣ ዲንጋዮች ተሰነጣጥቀዋል፣ የእርኩሳን መናፍስት፣ የመተት፣ የምዋርት ሥልጣን ተሽሯል። ስለዚህ ይህ ታላቅ ጸሎት በአጋንንት ላይ የበላይነት ስላለው በመጸለይ ራሳችንን ከአጋንንት ውጊያ ልንከላከልበትና ልናመልጥበት ብሎም አጋንንትን ልንቀጠቅጥበት ይገባል። በተጨማሪም ጻድቁ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዘወትር በትጋት ከሚጸልዩአቸው ጸሎቶች ውስጥ አንዱ ጸሎተ ባርቶስ እንደነበር ገድላቸው ይነግረናል። አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሀንም በዚህ ባርቶስ በተባለው ስፍራ ጸሎት ያደርሱ እንደነበር ተጽፏል። የእናታችን ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏🙏 ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በምንጸልየው ጸሎት ዓለምን ፈጥሮ ለሚገዛ፣ ፍጥረታቱን ለሚመግብ እኛን ከክፉ ለሚጠብቅ፣ የሚያስፈልገንን ሁሉ ለሚሰጠን አምላካችን ምስጋና የምናቀርብበት ነው፤ የእግዚአብሔርን ሥራ የምናደንቅበትም ነው፤ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹…አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለው..›› በማለት እንደገለጸው እግዚአብሔር በሕይወታችን ስለሚያደርግልን ነገር ሁሉ ምስጋና የምናቀርበው በጸሎት ነው፤ (መዝ.፶፪፥፱) ሌላው ደግሞ ከክፉ እንዲጠብቀን ሁል ጊዜ በጸሎት ልንማጸን ያስፈልጋል፤ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ምእመናን በላከው መልእክቱ ‹‹…በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር ጸልዩ..›› በማለት እንደመከረን ጠላታችን ዲያቢሎስ የሚያመጣብንን ፈተና በድል የምንወጣው ስንጸልይ ነው፡፡ (ኤፌ.፮፥፲፱) ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ጸሎትን መጸለይ እንዳለብን ያዘዘን (ያስተማረን) ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ጌታችን የጸሎትን ሥርዓት ያስተማረን ደግሞ በትምህርት ብቻ አይደለም፤ እርሱም ይጸልይ ነበር፤ ቅዱሳን ሐዋርያትንም እንዲጸልዩ ‹‹አባታችን ሆይ›› የሚለውን ጸሎት አስተምሯቸዋል፤ ‹‹…እናንተስ እንዲህ ጸልዩ…›› (ማቴ. ፮፥፱) እንግዲህ ልጆች! ጸሎት አስፈላጊ ነውና ልንጸልይ ያስፈልጋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጸሎት በሦስት ይከፈላል፤ የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት፣ የቤተ ሰብ ጸሎት በመባል ይታወቃል፤ እያንዳንዱ ክርስቲያን የሚጸልየው ጸሎት የግል ጸሎት ሲባል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚጸለየው የሚደርሰው ምስጋና፣ ሰዓታቱ ጸሎት፣ የማኅሌቱ፣ የጸሎተ ቅዳሴው፣ ምህላው ጸሎት የኅብረት ጸሎት ይባላል፤ ሌላው ደግሞ በቤተ ሰብ ውስጥ የሚደረገው ጸሎት ደግሞ የቤተ ሰብ ጸሎት ይባላል፡፡ ልጆች! እንግዲህ ክርስቲያን የሆንን ሁሉ በግል ሕይወታችን፣ በቤተ ሰብ እና በማኅበር ጸሎት ልንሳተፍ ያስፈልጋል፡፡ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! የጸሎት አደራረግ የራሱ ሥራዓት አለው፤ ውጫዊ እና ውስጣዊ ዝግጅት ያስፈልጉታል፤ ጸሎት ከማድረጋችን በፊት ንጽሕናችንን በመጠበቅ ነጠላችንን መስቀልያ፣ መልበስ፣ መብራት (ሻማ፣ጧፍ) ማብራት፣ በቅዱሳት ሥዕላት ፊት ቀጥ ብሎ በመቆም መዘጋጀት አለብን፤ እነዚህን በዋናነት ገለጽን እንጂ ሌሎችም ዝግጅቶች ያስፈልጋሉ፡፡ ውስጣዊ ዝግጅት የሚባለው ደግሞ ስንጸልይ በፍቅር መሆን አለበት፤ የምንለምነው እንደሚፈጸምልን ጽኑ እምነት ሊኖረንም ያስፍልጋል፤ በውጣችን ደግሞ ቂም በቀል መያዝ የለብንም፤ ምክንያቱም ልጆች ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርት ‹‹ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር ይላችኋልና›› በማለት እንዳስተማረን እኛ ‹‹ይቅር በለን›› ብለን ስንጸልይና ይቅርታን ስንለምን አስቀድመን ይቅርታ ማድረግ አለብን፡፡ (ማቴ.፮፥፲፬) ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በጸሎት ጊዜ ያለመታከት (ያለመሰልቸት) እና ባለመቸኮል መጸለይ አለብን፤ እንግዲህ ሰፊ ከሆነው የጸሎት ትምህርት ለግንዛቤ በማለት ጥቂቱን ብቻ ነገርናችሁ፤ ከዚሁ ጋር በተጓዳኝ ልብ ማለት ያለብን ነገር በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የጸሎት ጊዜያትም እንዳሉ ነው፤ በምን በምን ሰዓት ለጸሎት መቆም እንዳለብን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንማራለን፤ በቀጣይ ጊዜ እነዚህን የጸሎት ጊዜያትና ለምን እንደተወሰኑ እንመለከታለን፡፡ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! አባቶቻን በትምህርታቸው ‹‹ጸሎት የሕይወታችን አጥር ነው›› ይላሉ፤ የቤት አጥር ቤት በሌባ ከመዘረፍ እንደሚከልል ክርስቲያኖችም ደግሞ በሕይወታችን ጠላታችን ዲያብሎስ የሚያመጣውን ፈተናና መከራ የምንከላከልበት አጥር ነው፤ አባቶቻችን በጸሎት ጠላትን ድል አድርገዋል፤ ስለዚህ ጠዋት ስንነሣ ምንም ተግባር ከማድረጋችን በፊት መጸለይ አለብን፤ ውለን ወደ ቤት ስንገባ መጸለይ አለብን፤ ምግብ አቅርበን ከመመገባችን በፊት እንዲባረክልን መጸለይ አለብን፤ የሰጠንን አምላክ በጸሎት ማመስገን ያስፈልጋል፤ እንዲሁም ደግሞ ተመግበን ስንጨርስ (ስብሐት በማለት) ተመስገን ማለት አለብን፤ ማታም ከመተኛታችን በፊት መጸለይ ያስፈልጋል፤ ሌላው ከምንም በላይ በአሁን ጊዜ አገራችን ሰላም እንዲሆን፣ ፍቅርን እንዲሰጠን እግዚአብሔርን በጸሎት እንጠይቅ፡፡ Ethiopia ORTHODOX MEZMUR, መዝሙር፣ ስብከት mezmur orthodox ethiopian ethiopian orthodox mezmur mezmur orthodox orthodox mezmur Ethiopia ORTHODOX MEZMUR, መዝሙር፣ ስብከት mezmur orthodox ethiopian ethiopian orthodox mezmur mezmur orthodox
Ethiopia ORTHODOX MEZMUR, መዝሙር፣ ስብከት
mezmur orthodox ethiopian
ethiopian orthodox mezmur
mezmur orthodox
orthodox mezmur
Ethiopia ORTHODOX MEZMUR, መዝሙር፣ ስብከት
mezmur orthodox ethiopian
ethiopian orthodox mezmur
mezmur orthodox
orthodox mezmur
Ещё видео!