#የመዝሙሩ_ግጥም
✝️የጽዮን ደጆች✝️
የጽዮን ደጆች ቅኔን ተሞሉ
ለድንግል ክብር እልል እያሉ
እንደ ነጭ እንቁ የሚያበራ
አርፈናል ስሟን ስንጠራ(2)
ኃይልን በሚያደርገው ለተወዳጅ ስምሽ
የዜማ እቃችንን አነሳን ልጆችሽ
ማህተመ ቡራኬሽ በልባችን አለ
አፋችን ማርያም ሲል ጭንቃችን ቀለለ
የጽዮን ደጆች ቅኔን ተሞሉ
ለድንግል ክብር እልል እያሉ
እንደ ነጭ እንቁ የሚያበራ
አርፈናል ስሟን ስንጠራ(2)
የምስጋና ጥበብ የቅኔ ሃብት ፀጋ
ከደጃፍሽ መጥተን ገዛን ያለ ዋጋ
ጥልቁን ወጥተነዋል በትከሻሽ ሆነን
ፅዮንን በእልልታ በዜማ ሸፍነን
✝️እኔስ ተስፋ አልቆርጥም✝️
እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ሁሌ ጠራሻለሁ(2)
አማላጄ አንቺን ይዥለሁ
አዛኝቱ አንቺን ይዥለሁ
ዙርያዬን ሲጨልም ብርሃን ሆንሽኝ
ወዳጅም ሲከዳኝ አለው አልሽኝ(2)
ህይወቴ ከጥልቁ ማን መልሰው
ቀና ቀና ያልኩት በምልጃሽ ነው(2)
እኔስ ተስፋ አልቆርጥም ሁሌ ጠራሻለሁ(2)
አማላጄ አንቺን ይዥለሁ
አዛኝቱ አንቺን ይዥለሁ
✝️ከልጅነት አንደበቴ✝️
ድንግል ነች በሀሳብ በሕሊና
ያጌጠች በፍፁም ትህትና
ስላሴን በሆዷ አስተናግዳ
አየናት ምስለ ፍቁር ወልዳ
ከኪሩቤል ድንግል ትበልጣለች
ከሱራፌል ድንግል ትበልጣለች
ለእግዚአብሔር ቃል ማደሪያ ሆናለች
ከልጅነት አንደበቴ
አለኝ ምስጋና ለእመቤቴ
ከኮልታፋው አንደበቴ
አለኝ እልልታ ለእመቤቴ
ዚቅ ሚድያ ZIQ MEDIA “ለባለማህተቦች”
@ZIKMEDIA @ZIQRECORDS
Ещё видео!