Yehunie Belay SEKEN BEL | ሰከን በል! NEW Music 2016
ሰከን በል!
ይሁኔ በላይ አዲስ ነጠላ ዜማ
ዜማ:- ይሁኔ በላይ
ግጥም:- ፕሮፌሰር አዱኛ ወርቁ እና ይሁኔ በላይ
ሙዚቃ ቅንብር:- ሄኖክ ነጋሽ
ዋሽንት:-ጌታቸው ወርቅዬ
ተቀባይ:- መቅደስ መሸሻ
ድምጻዊ - ይሁኔ በላይ (ሰከን በል!)
ግጥም - (ፕሮፌሰር አዱኛ ወርቁና ይሁኔ በላይ)
ኸረ ተው በለው! ተው በለው!
ማንነቴን ብሎ ዓደባባይ ወጥቶ ባዶ እጁን እያየው፣
ሲያልፍ ለሚያልፍ ቀን ወንድሙን ወንድሙ አልሞ ገደለው።
ማንነት የራስ ነው፣ ሃይማኖት የግል ነው፣
አገር የጋራ ነው፣ ቁልፉና ማሰሪያው፣ ኢትዮጵያዊነት ነው።
በአዲሱ ዓመት፣ የለም መሞት፣
አበባ አደይ፣ ሞት ለገዳይ!
በመስከረም ኦሆሆ...በመስከረም ኦሆሆ... ፣
ሰለም ሰላም።
የመሰቀል ለታ፣ የመስቀል ለታ
በአንድ ገበታ።
በአዲስ ዘመን ኦሆሆ... ፣ በአዲስ ዘመን።
ኦሆሆ... ይብቃ ብለን።
ያ ወገኔ ዛሬ ምን አለ?
ኦሆሆ... አትንኩኝ አለ፣
ማንነቴን መልሱ እያለ፣
ኦሆሆ ... ሲዘምር ዋለ፣
ማንነቴን አልሸጥም አለ፣
ኦሆሆ... አይሻኝም አለ፣
ሥሙት ወገኔን አትተኩሱበት፣
እዩት ወገኔን አታፍጥጡበት።
በአዲሱ ዓመት፣አዲስ ብስራት፣
ሰከን ሰከን ሰከን ሰከን ሰከን በል
ሰከን በል ሰከን ማለት
ነው ጨዋነት፣
ሰከን ማለት ነው ጀግንነት፣
ወታደሩ ሰከን በል አፈመዙን ሰክን አድርገው፣
ቃታህንም እንዳትስበው፣ ባዶ እጁን ነው የሚጨው
ሰላማዊ ወንድምህ ነው፣ ሰከን በሉ ህዝቤን ተዉት፣
ድምፁን ሰሙት አትግደሉት።
መንግስት በሀገሩ በህዝቡ ላይተኩስ፣
''ዝ ኃጢያት ይኩን ውጉዝ ከማርዮስ''
ሰከን በል ተው ሰከን በል እንጅ
አንዱ ካንዱ ሳይበልጥ አንዱ ካንዱ ሳያንስ፣
አንዱ አንዱ ሳይገለው ደምም ሳፋሰስ፣
በወላጁ ጥፋት ልጅም ሳይወቀስ፣
ተባብሮ ተፋቅሮ በአንድነት መኖሩ
የጠቅመናል እንጅ ምንድነው ችግሩ?
ሰከን በል ተው ሰከን በል እንጅ
ድር እንኳን ቀጭኑ ድር እንኳን ለስላሳው፣
ሲያብር ሲተባበር ይበልጣል ካንበሳው፣
ስማኝ በጥሞና ልንገርህ ወገኔ፣
መለያየት ሞት ነው ላንተም ሆነ ለእኔ፣
ከታሪካዊዋ ከድንቅነሽ አገር፣
እምዬ ኢትዮጵያ ከሆደ ዥንጉርጉር፣
ቀይና ቀይ ዳማ ጠይምና ጥቁር፣
ወርቀዘቦ ሆነን አምረን ስንፈጠር፣
እንዴት እንለያይ በቋንቋና በዘር
ሰከን በል ተው ሰከን በል እንጂ
ሰከን ሰከን ሰከን
የወገን ጥያቄው ክብሩ ተመልሶ፣
በሰላም ለመኖር መግባባቱ ነግሶ፣
በስደት ያለውም ወደ አገሩ ገብቶ፣
በነፃነት ሊኖር እንደልቡ ገብቶ፣
እንደልቡ ወጥቶ፣
ተማምሏል ሕዝቧ ለአንዴና ለሁሌ፣
እልል እልል በሉ እንዲፈታ ሕልሜ፣
ሰከን በል ተው ሰከን በል እንጂ
ሰከን ሰከን ሰከን
እባክህ ጌታዬ ኢትዮጵያን ሕዝቦቿን ጠብቃት፣
የጦር መዝመቻ፣
የጠላት መዛበቻ፣
የመከራ መካተቻ
ከመሆን አድናት
አደራ እምዬን ኢትዮጵያን ጠብቃት።
Ещё видео!