ይህ ነው ፀሎቴ - ይስሐቅ ሰድቅ // Yih New Tselote by Yishak Sedik (Live Worship)
ይህ ነው ፀሎቴ የማይቀየረው
ምንም ቢሰጠኝ እጄ የማይለቀው
አጥብቄ የያዝኩት እንደ ቀሪ ሀብት
ራሴን እስካገኘው ሁሌም በአንተ ፊት
አንተን ፈልጌህ ነው!!!
የምታስፈልገኝ አንተው ነህ
እኔም የምፈልገው አንተን ነው
1/እህል ውሃ አይደለም ወይም መጠለያ
ለዘላለሙ አንተው ነህ የእኔ መኖሪያ
የምታስፈልገኝ አንተው ነህ
እኔም የምፈልገው አንተን ነው
ቃልህ ህይወቴ ነው ፊትህ ብርሃኔ
ኢየሱስ በአንተ ነውና የሆነው መዳኔ
የምታስፈልገኝ አንተው ነህ
እኔም የምፈልገው አንተን ነው
2/በውድቀት ሌሊት ነፍስ ስጋዬ አርፈው
መንፈሴ ግን ለአንተ ነቅቶ ነው ሚገኘው
የምታስፈልገኝ አንተው ነህ
እኔም የምፈልገው አንተን ነው
አለምን ያስንቃል ሀልዎትህ ገዝቶ
ካንተ ያጣብቃል ህይወት ሰማይ ገብቶ
የምታስፈልገኝ አንተው ነህ
እኔም የምፈልገው አንተን ነው
አንዴ ይነደሉ ቀላያት ያፍስሱ
በህይወት ውሃ ወንዝ ነፍሳት ይረስርሱ
ሰማዬ ሰማያት በቃ ይከፈቱ
አንተን ለማግኘት ነው ይህ ትውልድ ናፍቆቱ
የምታስፈልገን አንተ ነህ
እኛም የምንፈልገው አንተን ነው🙏
የሉቃስ ወንጌል 10
41፤ ኢየሱስም መልሶ አላት፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥
42፤ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም።
Ещё видео!