Medhane Alem School is one of the famous high school in Addis Ababa. I guess it's a childhood memory for many. I started working at Paulus Hospital and walked to Shegole, passing Filans, at the School of Medhane Alem. The morning sun was warming my back, but I tried to stop when I reached the school. The condition of the road was not very conducive to stopping.
I was happy and relaxed walk.
Medhane Alem School was founded by His imperial Majesty Haile Selassie I. It was the fourth Ethiopian modern school after Menilik II, Teferi Mekonnen and Empress Mennen School for Girls. It opened its doors as a boarding school, on Tikimt 27 1924 E.C. (October 17 1931) for 85 orphans to pursue academic & vocational training. The then famous architect, Lij Hailemariam Gezmu, was appointed as the first principal of the school. There were five Ethiopian, four French teachers and a large contingent of auxiliary staff.
By the way, the baby we see on the cover is kneeling at the door of the pharmacy. I tried to see what he wanted to see. TV is on and a movie is on. That was what the child saw. He is having fun in his own world.
መድሃኒአለም ትምህት ቤት ከአዲስ አበባ ታዋቂ ከሆኑት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዱ ነው፡፡ የብዙዎች የልጅነት ትዝታ እንደሆነ እገምታለሁ፡፡ ወክ ማድረግ የጀመርኩት ከፓውሎስ ሆስፒታል ሲሆን በመድሃኒአለም ትምህርት ቤት ፊላንስን አልፎ እስከ ሸጎሌ ነበር የተጓዝኩት፡፡ የጠዋቷ ጸሃይ ጀርባዬ እየሞቀችን ነበር የተጓዝኩት ግን መድሃኒአለም ትምህርት ቤት ጋር ስደርስ ቆም ለማለት ሞክሬ ነበር፡፡ የመንገዱ ሁኔታ ለመቆም ብዙም የሚያመች አልነበረም፡፡ ዘና እያልኩ ደስ እያለኝ ነበር የተጓዝኩት፡፡
መድኃኔዓለም ት/ቤት የተመሰረተው በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲሆን ከዳግማዊ ምኒልክ፣ ከተፈሪ መኮንን እና ከእቴጌ መንነን የሴቶች ትምህርት ቤት ቀጥሎ አራተኛው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ነበር። በጥቅምት 27 1924 (እ.ኤ.አ. ጥቅምት 17 1931) ለ85 ወላጅ አልባ ህጻናት የአካዳሚክ እና የሙያ ስልጠና እንዲከታተሉ እንደ አዳሪ ትምህርት ቤት በሩን ከፈተ። በወቅቱ ታዋቂው አርክቴክት ልጅ ኃይለማርያም ገዝሙ የትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ ርዕሰ መምህር ሆነው ተሾሙ። አምስት ኢትዮጵያውያን፣ አራት ፈረንሣይ መምህራን እና ብዙ ረዳት ሰራተኞች ነበሩ።
በነገራችን ላይ በከቨሩ ላይ የምናየው ህጻን ፋርማሲ በር ላይ ነው የተንበረከከው፡፡ ምን ማየት ፈልጎ ነው በሚል ወደውሰጥ ለማየት ሞክሬ ነበር፤ ቲቪ ተከፍቶ ፊልም ይታያል፡፡ ያንን ነበር ህጻኑ የሚያየው፡፡ እየተዝናና ነው በራሱ አለም፡፡
Ещё видео!